ውቧ ይርጋለም
ሲዳሞ ክፍለሀገር ዋና ከተማ የነበረችው ይርጋለም ስያሜዋን ያገኘችው በ1925 በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማ በራስ ደስታ ዳምጠው አማካይነት ነበር ፡፡
ውቧ ይርጋለም ከአዲስ አበባ 320 ኪሜ፣ ከሐዋሳ በ42 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች ፡፡ በአዲሱ መዋቅርና አስተዳደራዊ ፕላን መሠረት ከተማዋ ያረፈችው በ7ሺ ሄክታር ላይ ነው ፡፡ የመልክዓ ምድሯ አቀማመጥ ከባህር ጠለል በላይ…. ኪ.ሜ ከፍታ ላይ ይገኛል ።
የይርጋለም ቡና
በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ይርጋለም በቡና ምርት የምትታወቅ የግብርና ከተማ ነበረች።
ከ1940 እስከ እስከ 1970 መጀመሪያ ድረስ በቡና፣ በማር፣ በሰም፣ በእንስሳት ንግድ የተነሳ ከተማዋ የከፍታ ዘመኗ ነበር።
በመንገድ፣ በትምህርት ቤቶች ፣በሆስፒታል ፣ በቴሌኮሚኒኬሽን ፣ በውሃ፣ በመብራት፣ በመንግሥት ተቋማት ቀድማ የወጣችበትም ጊዜ ነበር።
ይርጋለም ካለፉት 55 ዓመታት ጀምሮ ከክፍለሀገር መቀመጫነት ወደ አውራጃነት ከዚያም ወደ ወረዳነት አሽቆልቁላ ነበር።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ አስተዳደራዊና ማህበራዊ እድገቶችን እያሳየች ትገኛለች። ከነዚህ መካከል ዋናዋናዎቹ
• የይርጋለም አግሮ እንደስትሪ ፓርክ
• የአዋዳ ዩንቨርሲቲ
• ይርጋለም ሜዲካል ኮሌጅ
• የይርጋለም ፓሊስ ማሰልጠኛ
• ፉራ የልማትና ጥናት ኢንሰቲትዩት
• የሙያና ቴክኒክ ማሰልጠኛ ኮሌጅ
• የአዋዳ ኢንደስትሪ ዞን እና ሌሎች ይገኙበታል።
ከ2015 ጀምሮ በአንድ አስተዳደር ከፍ ብላ ወደ ማዕከላዊ የሲዳማ ዞንነት ተሸጋግራለች።
በአሁኑ ጊዜ 80 ሺህ ሕዝብ በሰላም አቻችላ፤ አከባብራና አፋቅራ ታኖራለች። የከተማዋ መታወቂያ ልምላሜዋ ሲሆን ነዋሪዋ የዋህ ነው ። የሕዝቡ መታወቂያ የሆነው አንዱ አንጀት አርስ ሰላምታው
“ዳኤ ቡሹ !” ሲሆን ምላሹ ደግሞ “አኔራ ዳኤ ቡሹ !!” ይሰኛል🌹🥀🌾🌴